በማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሙስሊም ወጣቶች የካውንስሉን ቢሮ ጎበኙ
EMYC | ጥቅምት 19፣ 2019 ዓ.ል | ጁማደል አወል 18፣ 1448 ዓ.ሂ
በቲክቶክና በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ሙስሊም ወጣቶች መካከል የሆኑ ወጣቶች በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስልን ቢሮ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ዑስታዝ ሐይደር ከድር ካውንስሉ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራትና ስለሚሠራቸው ሥራዎች ለወጣቶቹ ገለጻ አድርገዋል።
ወጣቶቹም ካውንስሉ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት መደነቃቸውን በመግለጽ፣ ወደፊት በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በካውንስሉ ስለሚከናወኑ ሥራዎች ግንዛቤን ማሳደግ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የትብብር ዕድሎችን ማስፋት እንዲሁም የተቋሙን መልካም ሥራዎች ለሰፊው ማኅበረሰብ ማድረስ ነው