ወጣት ሙፍቲ ሐሊፋ አሰማኒ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስልን ቢሮ ጎበኙ!
EMYC | ጥቅምት 20፣ 2019 ዓ.ል | ጁማደል አወል 19፣ 1448 ዓ.ሂ
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዚዳንት ሙፍቲ ሐሊፋ አሰማኒ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስልን ቢሮ ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት በካውንስሉ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ፣ በክልሉ የሚከናወኑ ተግባራትና በተቋማዊ አሠራር ላይ ያተኮረ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከካውንስሉ ፕረዚዳንት ዑስታዝ ሐይደር ከድር ጋር ውይይት አድርገዋል።
ጉብኝቱ በካውንስሉ ማዕከላዊ መዋቅርና በክልሉ አመራር መካከል ያለውን የሥራ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ነው።